የፒኝኬው ልማት ማህበር 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን በጋምቤላ ከተማ አካሄደ ።
ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት (ነሀሴ 17/2017) ዓ.ም
የማህበሩ የ12 ወራት እቅድ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
በበጀት አመቱ የፒኝኬው ልማት ማህበር የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ ዕቅዶችን በማቀድ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተገልጿል።
በሪፖርቱ እንደቀረበው የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ ከክልሉ ብድርና ቁጠባ ተቋም እንዲሁም ሜርሲ ኮርፕስ ከተሰኘው ግብር ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር የትራክተር ግዢ መፈፀሙ ተመላክቷል።
በፒኝኬው ቀበሌ ከስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር እንዲሁም ማህበሩ ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ በመሆን የሀብት ማሰባሰብ ስራ በመስራት የውሀ ተቋም መገንባቱ ተገልጿል።
እንዲሁም አቅም ለለላቸው ተማሪዎች የገንዘብ እንዲሁም የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ኡቦንግ ኚጎዎ እንደገለፁት የፒኝኬው ልማት ማህበር የተቋቋመበትን አላማ በተፈለገው መንገድ ማሳካት እንዲችል የማህበሩ አባላት በቁርጠኝነት መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በተለይም የማህበሩን የፋይናንስ አቅም ከማሳደግ አኳያ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በቀጣይም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና የፋይናንስ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
